1. ይዘት
  2. ቀዘፋ
  3. ተጨማሪ ይዘቶች
  4. አብሮ መቅዘፍ
  5. ፍለጋ
  6. ከ 30 ቋንቋዎች ይምረጡ።

 
 
 

 

ባሕል እና ሌሎች | 19.11.2008

ማማ አፍሪቃ፣ ማርያም ማኪየቫ

በአለም አቀፍ ደረጃ ታላቅ ታዋቂነትን ያተረፈችዉ የደቡብ አፍሪቃዊትዋ ማሪያም ማኪየቫ በድንገተኛ የልብ ህመም ከዚህ አለም በሞት ተለይታለች። ማማ አፍሪቃ በመባል የምትታወቀዋ የደቡብ አፍሪቃዊቷ ታዋቂ ሙዚቀኛ ማሪያም ማኪየቫ የሰባ ስድስት አመት አዛዉንት ነበረች።

ትዉልዷ እ.አ የካቲት 25 / 1932 በደቡብ አፍሪቃ ጆሃንስበርግ አካባቢ ባለች መንደር እንደሆነ የሚነገርላት ማርያም ማኪየቫ፣ በተስፍ እና በቁርጠኝነት በምታቀነቅናቸዉ ዜማዎችዋ በደቡብ አፍሪቃ አፓርታይድን በመቃወም እንቅስቃሴዋን ዳር አድርሳለች። ባለፈዉ ሳምንት መጀመርያ ላይ ማርያም ማኪየቫ በደቡብ ጣልያን የሙዚቃ ስራዋን ካሳየች በኻላ በልብ ድካም ህመም እስከ መጨረሻ ዝምታን መርጣ አለምን ተሰናብታለች። ማርያም ማኪየቫ የኢትዮጽያዉ የሙዚቃ ንጉስ የዶክተር ጥላሁን ገሰሰ ሙዚቃን በማዜሙዋ በአራችን ታዋቂነትን እና ይበልጥ ተወዳጅነትን አትርፋለች። በተጨማሪ ማርያም ማኬየቫ ታዋቂዋን ኢትዮጽያዊ አቀንቃኝ ሜሪ አርምዴን በግል በኢትዮጽያ ተገኝታ መጎብኘትዋም ይነገራል። የባህል መድረጋችን ሰፋ ያለ ጥንቅር አለዉ ያድምጡ   

 
 
መጣጥፍ መጽሐፍ ማቅለም

ምላሽመላክማተም

ተጨማሪ አርእስተ-ዜና



 

DW-TV EUROPE live

Journal (deutsch) - Mit Tagesthema