የኢትዮጵያ ትምሕርት ሚኒስቴር ከ 2003 ዓም ጀምሮ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ይሰጥ የነበረው የርቀት ትምሕርት ሙሉ በሙሉ እንዲቋረጥ ያወጣው መመሪያ እያነጋገረ ነው ።
የትምሕርት ሚኒስቴር መመሪያው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየወረደ የመጣውን የትምሕርት ጥራት ደረጃ ለማሻሻልና ከሐገሪቱ የሰለጠነ የሰው ኃይል ፍላጎት ጋር የሚጣጣም ዓለም ዓቀፍ ደረጃን የጠበቀ ሰልጠና ለመስጠት ያለመ መሆኑን ገልጿል ። በአንፃሩ እገዳው ያለ ቅድመ ማስጠንቀቂያ መጣሉን የሚቃወሙት የግል ዩኒቨርስቲዎች ና ኮሌጆች የትምሕርት ደረጃን ለማስጠበቅ ዓለም ዓቀፍ መስፈርትን አውጥቶ መስራት እንጂ መመሪያ ጥራት ማስጠበቅ አይችልም ሲሉ ይከራከራሉ ።
ታደሰ እንግዳው
ሂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ