ትናንት እዚህ ጀርመን ገበያ ላይ የዋለው የጀርመን ቡንደስ ባንክ የቦርድ አባል የቲሎ ዛራትሲን መጽሐፍ ጀርመን ውስጥ አሁንም የመነጋገሪያ ርዕስ ሆኖ እንደቀጠለ ነው ። “
ጀርመን ራሷን ለውደቅት እየዳረገች ነው” የሚል ሀሳብ የያዘው የዚህ መፀሀፍ ደራሲ የእስልምና ባሕል ጀርመን የሚኖሩ ሙስሊሞች ከህብረተሰቡ ጋር ተዋህደው እንዳይኖሩ እንቅፋት ሆኗል ሲሉ ተችተዋል ። ጀርመን ከሚኖሩ የውጭ ዜጎች በተለይ ሙስሊሞች ከህብረተሰቡ ጋር ባለመዋሀዳቸው ምክንያት ሀገሪቱን ከመጥቀም ይልቅ ሸክም እንደሆኑባት በመፀሀፋቸው ያካተቱት ሀሳብ ሙስሊሙን ህብረተሰብ በእጅጉ አስቆጥቷል ። ከጀርመንዋ መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል አንስቶ የጀርመን ፖለቲከኞችም የዛራትሲንን ሀሳብ ተቃውመው አስተያየታቸውን እየሰጡ ነው ።
ሂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ
ሸዋዮ ለገስ