ባለፈው የጎርጎሮሳውያኑ 2009 ዓ.ም መጨረሻ ላይ አዲሱን የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ሥልጣን የያዙት ብሪታኒያዎቷ ካትሪን አሽተን አውሮፓ በቻይናና በህንድ ተገፍታ ከዓለም ትኩረት ከመገለሏ በፊት የውጭ መርሀችንን እናስተካክል ሲሉ አስጠንቅቀዋል
። አሽተን ከአዲሱ ሥልጣናቸው የአንድ መቶ ቀናት ቆይታ በኃላ ለአውሮፓ ህብረት ፓርላማ ያስተላለፉት ማሳሰቢያ የዛሬው አውሮፓ ጀርመን ዝግጅታችን ትኩረት ነው ። የጀርመን ዜግነትን ለማግኝት የሚያመለክቱ የውጭ ዜጎች ቁጥር ከቀድሞው እየቀነሰ ነው ። ለዚህ ዓብይ ምክንያት የተበለው ከ3 ዓመት ወዲህ ተግባራዊ የሆነው በአዲሱ የጀርመን የዜግነት አሰጣጥ ህግ ውስጥ የተካተተው የዜግነት ፈተና ነው ። በዛሬው አውሮፓ እና ጀርመን ዝግጅት ከሚነሱት ነጥቦች አንዱ ነው ። የላትቪያ ፓርላማ በቅርቡ ያፀደቀው አወዛጋቢው የውጭ ዜጎች እና የስደተኞች አዲስ ህግም ዛሬ ጊዜ ከተያዘላቸው መሰናዶዎች አንዱ ነው ።
ሂሩት መለሰ ፣
ነጋሽ መሀመድ